Sunday, October 11, 2020

የኦንላይን ስራ ምንድን ነው?

የኦንላይን ስራ ምንድን ነው?
https://kol.jumia.com/api/click/banner/a306939d-b3a9-4ea9-82b1-175f7d1a683a/1625c9fa-d637-4443-a62a-c3858baa4c55/?utm_campaign=a306939d-b3a9-4ea9-82b1-175f7d1a683a በኦንላይን ወይም በኢንተርኔት ከቤታችን ሆነን የምንሰራቸው ስራዎች ማለት ወደ ቢሮ ወይም ስራው የሚሰራበት ቦታ መምጣት ሳያስፈልግ እዛው እቤታችን ሆነን በኢንተርኔት ተጠቅመን መስራት እና ስራውን ሰርተን ማስረከብ ነው፡፡ 
ከዛ ለስራው የሚገባውን ክፍያውን ወይም የተስማማነውን ክፍያ ወይ በባንክ ወይንም በሌላ የመክፈያ ዘዴ መቀበል ማለት ነው፡፡እነዚህ ስራዎች ምን አይነት ናቸው…
ለምሳሌ፡- 
 የትርጉም ስራዎች፡- ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ፤ ከኦሮምኛ ወደ ትግረኛ፤ከአማርኛ ወደ ጉራግኛ ፅሁፎችን ተርጉሞ ታይፕ አርጎ መላክ   
 ታይፕ ማድረግ(ትራንሲክሪፐሽን)፡- ተቀድቶ በድምፅ ተልኮ እሱን ታይፕ አርጎ መላክ 
 ዳታ ኢንትሪ (መረጃን መመዝገብ)፡- በወረቀት ላይ መረጃው ተሞልቶ ሊሰጠን ይችላል ወይም በተለያየ መንገድ መረጃው ይሰጠናል፡፡ ያንን ኮምፒውተር ላይ ማስገባት ወይም ደንበኞቹ በሚመርጡት የዳታ ሶፍትዌር ውስጥ መመዝገብ ማለት ነው፡፡ 
 ዌብ ዴቨሎፕመንት፡- ለድርጅቶች ወይም ለሰዎች ዌብሳይታቸውን ወይንም የሶሺያል ሚዲያ ገፆቻቸውን መስራት፡፡ 
 የፅሁፍ ስራዎች፡- ለተለያዩ ዌብሳይቶች፤ ብሎጎች፤ መፅሄቶች የሚሆኑ ፅኁፎችን መፃፍ
 እነዚህ እና እደነዚህ አይነት ስራዎች ናቸው እንግዲህ በኦንላይን የሚሰሩት ማለት ነው፡፡ 

ስለኦንላይን ስራዎች ብዙ ማስታወቂያዎች በተለይ በሶሻል ሚዲያ ላይ ልናይ እንችላለን፡፡ እዚህ ላይ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ 
ለምሳሌ ሰሞኑን በኢሜል ብዙዎቻችን ጋር የደረሰ ነገር አለ፡፡ ኢሜሉ ላይ ከቤት በኢንተርኔት ልንሰራው የምንችለው ስራ እንዳለ ይገልፃል፡፡ እና ኢሜሉ ላይ ሊንክ ተካቷል፡፡ያንን ሊንክ ስንጠቀም ወደ ዌብሳይቱ ይወስደናል፡፡ እነዚህ ዌብሳይቶች መኒ የሚል ነገር ስማቸው ላይ ይኖራል፡፡ ለምሳሌ፡- xfu money or xyz money or ber money club የሚል ስም ይኖራቸዋል፡፡ 

በአብዛኛው እነደነዚህ አይነት ዌብሳይቶች ኢንተርኔት ላይ ማስታወቂያዎችን በማየት ብር ማግኘት እንደሚቻል ነው የሚነግሩን፡፡ ወደ ዌብ ሳይቶቹ ከገባን በዃላ የምናያቸው ነገሮች 
1. የመጀመሪያው የፊት ገፅ ላይ የተለያዩ የግለሰብ ስሞች እና ዌብ ሳይቱን በመጠቀም በሳምንት/ በወር ያገኙት የገንዘብ መጠን ተፅፎ እናያለን፡፡ ገንዘቡ እንደተከፈላቸው ያሳያል 
2. በቀን ከ3 እስከ 5 ሰአታት ከሰራን ከ50 እስከ 300 ዶላር ማግኘት እንደምንችል ያሳያል 
3. ከዛ ያው ኢሜል በመጠቀም ሬጅስተር እንድናደረግ ነው የምንጠየቀው፡፡ሬጅስተር ካደረግን በዃላ ማስታወቂያዎቹን እያየን በኛ ስም ስር ያለው የገንዘብ መጠን ያድጋል፡፡ ወዲያው ነው ብሩ የሚበዛው እና እውነት ሊመሰል ይችላል፡፡ 
4. ከዛ ብሩን ለማውጣት ስንሞክር የሚያጋጥመን 
 መጀመሪያ እነዚህ ዌብ ሳይቶች ላይ ስንመዘገብ ብሩን (የሰራንበትን ብር) በፈለግንበት መንገድ እንደሚልኩልን ነው የሚነግሩን፡፡ ማለትም ባንክ አካውንታችን ውስጥ እንደሚያስገቡልን ወይም በዌስተረን ዩንየን እንደሚልኩልን 
 አካውንታችሁ አፕሩቭ እስኪደረግ ከ30 እስከ 60 ቀን ይፈጃል፡፡ ቶሎ ብራችሁን ማግኘት ከፈለጋችሁ ግን ብለው የክሬዲት ካርድ መረጃ ወይንም የቢት ኮይን አካውንት ቁጥር ይጠይቃሉ፡፡ ሃሳቡ ያው ያለንን ብር ወይም መረጃ ለመስረቅ ነው፡፡ 
 አንዳንዴ ደግሞ ብር ለማግኘት ቢያንስ ለ30 ወይም ለ40 ሰው ይሄንን ኢሜል ላክ ሊሉ (ሪፈራል) ይችላሉ፡፡ ይህም የሌላን ሰው መረጃ ወይም የኢሜል አድርሻ በኛ በኩል ለማግኘት ነው እንጂ ለ40 ሰው ስለላክን ይከፍሉናል ማለት አይደለም፡፡ 

5. እንድነዚህ አይነት ሳይቶች የውሸት ናቸው፡፡ መረጃን ለመስረቅ፤ እኛ የምንጠቀምበት ኔትወርክ ውስጥ ለመግባት/ሃክ ለማድረግ ሊሆን ይችላል እና ሊንኩን ባንጫን እና ወደ ዌብ ሳይቱ ባንሄድ ነው የሚመረጠው፡፡

ስለዚህ ከነዚህ አይነት በኦንላይን ስራ ስም ከሚደርጉ ማጭበርበሮች በጣም መጠንቀቅ ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ 
በቀላሉ እንደ እነዚህ አይነት ማታለያዎችን ማወቅ እና መጠንቀቅ እንችላለን፡፡ 
1. ድርጅቱን ወይም ዌብ ሳይቱን ጉግል ካደረገነው በቀላሉ ከታመኑ ምንጮች መረጃዎችን ስለድርጅቱ ወይም ስለ ዌብ ሳይቱ ማግኘት እንቻላለን፡፡ ቅድም ሳነሳው የነበረው xyz money ጉግል ብናደርግ የማጭበርበሪያ ዘዴ መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡ 
2. ሌላው የስራው ማስታወቂያው ግልፅ አይደለም፡፡ ከቤት በኢንተርኔት ለሚሰራ ስራም ቢሆን ወይንም ቢሮ ውስጥም ተቀጥረን ለምንሰራው ስራ ቀጣሪዎች ሁል ጊዜ የምንሰራው ስራ ምን እንደሆነ በዝርዝር ይናገራሉ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አለ የተባለው ስራ የውሸት ሊሆን ስለሚችል መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ 
3. ማስታወቂያው ላይ ብዙ ክፍያ እንከፍላን የሚል ከሆነ መጠራጠር ይኖርብናል፡፡ ገበያው ላይ ያለውን ክፍያዎች እናውቃለን ስለዚህ ለየት ያለ ከፍተኛ የሆነ ክፍያ እንሰጣለን ሲሉ በጥንቃቄ ልናየው ይገባል ማለት ነው፡፡ 
4. በኢንተርኔት የምናነበው ወይም የምናየው ነገር ሁሉ እውነት አይደለም:: በተለይ ደግሞ እንደዚህ አይነት ዌብ ሳይቶች ላይ ምስክርነቶች ይካተታሉ፡፡ ሰዎች በቪድዮ እየቀረቡ ወር ይሄን ያህል ብር ሰራሁ፤ በሳምንት ይሄንን ያህል ብር ሰራሁ፤ በዚህ ዌብሳይት ምክንያት ከድህነት ወጣሁ እና የመሳሰሉትን ነገሮች ያወራሉ፡፡ በቪዲዮ ብቻ አይደለም አንዳንዴ ደግሞ በፅሁፍም ያቀርቡታል እና እነዚህን ነገሮች ማመን የለብንም፡፡
Share:

0 comments:

Post a Comment

ad

https://kol.jumia.com/api/click/banner/a306939d-b3a9-4ea9-82b1-175f7d1a683a/1625c9fa-d637-4443-a62a-c3858baa4c55/?utm_campaign=a306939d-b3a9-4ea9-82b1-175f7d1a683a

BTemplates.com

Followers

Followers